Duration 5:12

ሀገሬ በሰማይ Hagere Besemay ዮሴፍ በቀለ Yosef Bekele

Published 1 Jan 2022

Gospel song by singer Yosef Bekele. My permanent place/home is in heaven. An everlasting home owned through Jesus' work. I have nothing on this earth. I am here just temporarily. “አገር አለኝ” በዘማሪ ዮሴፍ በቀለ እሄዳለሁ ሀገሬ ጌታዬን አየዋለሁ ላየው ፊት ለፊቱ ሀገር አለኝ እኔስ በሰማያት በጉ ብርሃኑዋ (የሆነላት) 2 ሀገር አለኝ እኔስ በሠማያት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ (ያዘጋጃት) 2 እንግዳ ነኝና (አልሆንም ቤተኛ) 2 ሀገሬ ሰማይ ነው በላይ ርስት አለኛ በላይ ቤት አለኛ ተዘጋጅቼ ልጠብቀው ቤቴን ሌት ተቀን ላሰናዳው [ይመጣል! ጌታ ይመጣል! ይመጣል! እርሱ ይመጣል!] 2 አሃሃሃ አልዘናጋም አሃሃሃ ጠፊውን አይቼ አሃሃሃ በላዬ ላከማች አሃሃሃ ልስራ ተግቼ አሃሃሃ እርሱ ይመጣል አሃሃሃ ወይ እሄዳለሁ አሃሃሃ እንደስራዬ አሃሃሃ እቀበላለሁ ዓይን ያላያት የሰው እጅ ያልሰራት ለልጆቹ ጌታ ያዘጋጃት (ሀገር አለኝ እኔስ በሰማይ) 2 የቅዱሳን የጻድቃን ከተማ ቀኑ ቀርቧል ወደዚያ ልገባ (ሀገር አለኝ እኔስ በሰማይ) 2 መታረዝ መራቆት መራብም ያልፍና ሰቆቃው ሐዘኑ ሁሉ ይረሳና ጌታዬን ፊት ለፊት በክብር አያለሁ ናፍቆቴን ደስታዬን ያኔ እወጣለሁ [ይመጣል! ጌታ ይመጣል! ይመጣል! እርሱ ይመጣል!] 2 የፍጻሜው መለከት ይነፋል ጌታ ኢየሱስ በክብር ይመጣል (ሀገር አለን እኛስ በሠማይ) 2 በቅጽበት ዓይን ሁሉ ይለወጥና እንሄዳለን ልንኖር ከእርሱ ጋራ (ሀገር አለን እኛስ በሠማይ) 2 የዚህ ዓለም ነገር አላፊ ጠፊ ነው ውበት ደም ግባትም ሁሉ ረጋፊ ነው ጌታዬን ሲመጣ እንዳየው ሳላፍር ሥጋዬን ልጐስም ልኑር ለእርሱ ክብር [ይመጣል! ጌታ ይመጣል! ይመጣል! እርሱ ይመጣል!] 2 እዚህ ነዋሪ (አይደለሁም) 2 እንግዳ ነኝ እኔ ቆይታዬ ያበቃና ይፈጸማል እሄዳለሁ ሀገሬ ሀገሬ በሰማይ ሀገሬ ሀገሬ በላይ ነው ሀገሬ (ሀገሬ በሰማይ ሀገሬ ሀገሬ በላይ ነው ሀገሬ) 2

Category

Show more

Comments - 3